ሀገራዊ ምክክሩ በውይይት የጋራ መግባባት ለመፍጠር ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ ፈጥሯል- አምባሳደር መሐሙድ ድሪር
ሀገራዊ ምክክሩ በውይይት ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሐሙድ ድሪር፤ ኢትዮጵያ በምክክር ችግሮቿን ለመፍታት የነበሯት በርካታ ዕድሎችና አጋጣሚዎች አምልጠዋት እስካሁን መዝለቋን አስታውሰዋል። በተለያዩ ዘመነ-መንግሥታት ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ሰፊ ዕድል የነበራት ቢሆንም ወደ ተግባር መቀየር ተስኗት መቅረቱንም ይናገራሉ። ለአብነትም…
