የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የኢትዮጵያ ባንኮች ህልውናን ያስቀጠለ ነው-ጠ/ ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የኢትዮጵያ ባንኮች ህልውናን ያስቀጠለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ትናንት በሰጡት ማብራሪያ÷ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ዝግ አድርጋ መቆየቷ ለዘመናት ፈተና ውስጥ እንድትወድቅ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም የወጪ ንግዱ የሚፈለገውን ያህል የውጭ ምንዛሬ ማስገባት ተስኖት መቆየቱን ጠቅሰው፤ የኢትዮጵያ ምርቶችም በኮንትሮባንድ እንዲወጡ ማድረጉን ነው ያነሱት፡፡ ኢትዮጵያ…
