Trendings

ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ በዲጂታል ሚዲያው እየተሰራጩ ካሉ ሀሰተኛ መረጃዎች ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አሳሰበ

ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ በዲጂታል ሚዲያው ላይ እየተሰራጩ ያሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የኢፌዲሪ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አሳስቧል፡፡ አካባቢያዊ፣ ክልላዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ይፋዊ ግንኙነቶች በጽህፈት ቤቱ ይፋዊ የዲጂታል አማራጮች ብቻ እንደሚሰራጩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የፅህፈት ቤቱን ሎጎ አላግባብ በመጠቀም የውሸት መረጃዎችን ከሚያሰራጩ አካላት ማህበረሰቡ እራሱን እንዲጠብቅም አሳስቧል፡፡

Read More

በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ስኬት በማስቀጠል ከተረጂነት መላቀቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው – ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ስኬት በማስቀጠል ከተረጂነት መላቀቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ዘርፈ-ብዙ ጸጋዎች ያሏት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ጸጋዎች በሚፈለገው ደረጃ ወደ ልማት መቀየር አለመቻላችን ደግሞ ከተረጅነት እንዳንወጣ አድርጎን ቆይቷል ነው ያሉት፡፡ አሁን ላይም ያሉንን ጸጋዎች በማልማት ከተረጂነት ወደ…

Read More

ምክር ቤቱ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ

የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ ዘርፉን በማዘመን ዓለም አቀፍ ትስስርና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጂጌ ገልጸዋል። የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ ዘርፉን በማዘመን ዓለም አቀፍ ትስስርና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ…

Read More

የህዝቦች የወል ታሪክ ለጠንካራ የሀገር መንግስት ግንባታ ያለውን ሚና በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ

የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የታሪክ ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር “ታሪክ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት ግንባታ” በሚል መርህ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም፤ የሀገር ግንባታ ሥራ ከታሪክ አስተምህሮ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ትውልዱ የትናንቱን ታሪክ ተረድቶ ከዛሬው ጋር እያቆራኘ እንዲሄድና እሴቱን እንዲጠብቅ የታሪክ ባለሙያዎች ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ተናግረዋል። በተለይ የህዝቦች የወል ታሪክ ለጠንካራ የሀገር…

Read More

ምክር ቤቱ የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን የወጣውን የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ። ምክር ቤቱ ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባው የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና የልማት ተነሺዎች የሚቋቋሙበት ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል። ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በአብላጫ ድምጽ አድቋል። የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች…

Read More

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በመጪው በጀት ዓመት የ8 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ግብ ተይዟል – ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)

በ2017 በጀት ዓመት ሀገራዊ ጥቅል ኢኮኖሚው የ8 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት እንዲያስመዘግብ መታቀዱን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) ገለጹ። መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድን መገምገሙ ይታወቃል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) ለኢዜአ አንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ባለፉት 10 ወራት በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች በዓመቱ የ7 ነጥብ 9 በመቶ…

Read More

መንግሥት ለመመካከር እና ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ደጋግሞ ገልጿል- አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር

በአማራ ክልል ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያየዘ መንግሥት ለመመካከር፣ ለመወያየት እና ለንግግር ዝግጁ መሆኑን ደጋግሞ ሲገልጽ ቆይቷል ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡ በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ ”ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡ በኮንፈረንሱ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና…

Read More

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ የመቋቋም ጥረት ሁነኛ ማሳያ ነው

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ የመቋቋም ጥረት ሁነኛ ማሳያ መሆኑን በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አግነስ ኪጃዚ (ዶ/ር) ገለጹ። በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ቀጣይነት ያለው ጥረት በተመለከተ ዋና ዳይሬክተሯ አግነስ ኪጃዚ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም ዓለም አቀፍ ስጋት በሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ በተለይም የአፍሪካ አገራት…

Read More

በአራት ክልሎች የተካሄደው የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በተሳካ መልኩ ተጠናቋል፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በአራት ክልሎች የተካሄደው የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት በተመለከተም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ መግለጫ ሰጥተዋል። በ6ኛ ዙር ጠቅላላ ሀገራዊ…

Read More

የሆርቲካልቸር ምርቶችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳልጥ ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል

ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ የምታቀርባቸውን የሆርቲካልቸር ምርቶች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትና ጥራትን ጠብቀው እንዲቀርቡ ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ መደረጉን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ። በምርት ጥራትና ደህንነት ላይ ያተኮረ ብሔራዊ የምርት ጥራት ምዘና ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሒዷል። ጉባኤው በኢትዮጵያ ተመርተው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የሆርቲካልቸር ምርቶችን የጥራት ደረጃ የሚጠበቅበትንና ተወዳዳሪነታቸው የሚጨምርበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ግብርና…

Read More