Trendings

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በተፈጸመ ዝርፊያ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሷል፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በተፈጸመ ዝርፊያ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አበበ ተስፋ እንደገለጹት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ እየተፈጸመ ያለው ዝርፊያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በ2016 ዓ.ም ብቻ ከሦስት መቶ በላይ ዝርፊያዎች የተፈጸሙ ሲሆን ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ በተቋሙ ሃብት ላይ ኪሳራ…

Read More

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነትና ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች – አቶ አደም ፋራህ

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነትና ትብብር በሁሉም ዘርፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ። በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ከሰኔ 9 እስከ 12 ቀን2016 በሚካሔደውና “ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር” በሚል መሪ ሃሳብ በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች…

Read More

የበጀት ዓመቱ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና የዘር ሽፋን ከፍተኛ ለውጥ የተመዘገበበት ነው – ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)

የበጀት ዓመቱ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና የዘር ሽፋን ከፍተኛ ለውጥ የተመዘገበበት መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለጹ። የበጀት ዓመቱ የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል። በመድረኩም የግብርና ስራዎች አፈፃፀም በስፋት ውይይት የተደረገበት መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገልጸዋል። የ2015/16 የምርት ዘመን ከታቀደው እቅድ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ምርት የተሰበሰበበት መሆኑንም አንስተዋል። በተለይም…

Read More

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን መገንባት የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት የጤና ሚኒስቴርና ሌሎች ሦስት ተቋማት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ። ሥምምነቱን የጤና ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲና የሩስያ ፓን-አፍሪካ ፐብሊክ ፕራይቬት አጋርነት ለልማት የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ተወካዮች ፈርመውታል። የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚህ ጊዜ፤ በሥምምነቱ መሠረት ፕሮጀክቱ ለአምስት ዓመታት እንደሚቆይና 2 ሺህ የጤና ማዕከላትን ለመገንባት…

Read More

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ የሲቪል ሰርቪሱን የማስፈጸም አቅም ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ የሲቪል ሰርቪሱን የማስፈጸም አቅም ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና ምርታማነትን ለመጨመር እንደሚያስችል ተመላከተ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010ን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት መድረክ አካሂዷል። የአዋጁን ማሻሻል አስፈላጊነት፣ ዓላማ፣ ይዘት፣ ተፈጻሚነትና ሌሎች አጠቃላይ የአዋጁ ድንጋጌዎች…

Read More

ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ ተጠቃሚነቷ እንዲረጋገጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥናት ለመደገፍ እየተሰራ ነው

ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ተጠቃሚነቷ እንዲረጋገጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥናት ለመደገፍ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለጸ። በኢንስቲትዩቱ የኤዥያና ፓሲፊክ ጉዳዮች ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ጌታቸው(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ አንዱ ነው ብለዋል። ይህንን ከግምት በማስገባት ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስከበር ጎን ለጎን የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው…

Read More

የሲንጋፖር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

የሲንጋፖር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል በመጠቀም በኢትዮጵያ በግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሲንጋፖር አቻቸው ቪቪያን ብላከሪሽናን (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው እንዲሁም የጋራ ትብብርን…

Read More

ኢንስቲትዩቱ የቲቢ ህክምናን ከ24 ወራት ወደ 9 ወራት ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት ማግኘቱን አስታወቀ

የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት 24 ወራት ይወስድ የነበረውን መድሃኒት የተላመደ የቲቢ ህክምናን ወደ ዘጠኝ ወራት ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ 54ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የጉባኤና ጉብኝት መርሃ ግብር የጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት፣ የልማት አጋሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል። መርሃ ግብሩ ኢንስቲትዩቱ በምርምር ያለው አበርክቶና በሚያከናውናቸው ስራዎች ዙሪያ ገለጻ በማድረግ…

Read More

የጃንቹ ተራራና የሙዝ ደን

የወረዳው ሕዝብ የመንግስትን የልማት አቅጣጫ ተቀብሎ የመተግበር ልምድ ያዳበረ ለመሆኑ ማሳያ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን በሁሉም ወረዳዎቹ ተመሳሳይ ምርት የሚመረትበት ነው። ይህ የሙዝ ምርት የሚዛን አማን ከተማን ጨምሮ በሌሎች ወረዳዎችም ይመረታል። የምርቱ መጨመር የአካባቢ የሙዝ ገበያን አረጋግቷል። ለአብነትም በሚዛን አማን ከተማ አራቱ በ20 ብር ሲሸጥ የነበረ የበሰለ ሙዝ አሁን በግማሽ ቀንሶ በ10 ብር እየተሸጠ ነው።…

Read More

32ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ከህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ…

Read More