Trendings

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የሚያቋቁሙት የኮሪደር አስተዳደር የወደብና የትራንስፖርት አገልግሎት ቀልጣፋ እንዲሆን ያስችላል ተባለ

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ በጅቡቲ ወደብ ላይ የአሰራር አለመቀላጠፍ ከገጠመ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ተወዳዳሪነት ላይ ትልቅ ተጽእኖ ይኖረዋል። ወደ ሀገር የሚገቡና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች በጅቡቲ ወደብ በኩል እንደሚተላለፉ ጠቅሰው፤ የወደብ አገልግሎቱ ቀልጣፋ ካልሆነ ምርቶች በውጭ ገበያ የመወዳደር ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ የወጪ እና ገቢ ንግዱን እንዲሁም በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከውጭ ጋዜጠኞች ጋር ውይይት አካሄደ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል በኢትዮዽያ በሥራ ላይ ካሉ ታላላቅ አለምአቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የውጭ ጋዜጠኞችን ሚዛናዊ እና ተጨባጭ የዘገባ ሽፋንን ለማሳደግ አላማ ያደረገ ውይይት አካሂዷል። ኢትዮጵያ ፈጣን የለውጥ እና ልማት ሂደት ውስጥ እንደመገኘቷ ጋዜጠኞች የተጠራ መረጃ ብሎም ዝርዝር ግንዛቤ ማግኘታቸው እጅግ አስፈላጊ ነው። መሰል ግንኙነቶች በኢትዮዽያ ላይ ያተኮሩ የዜና ሽፋኖች የኢትዮጵያን እድገት…

Read More

የዩናይትድ ኪንግደም የግብርና ንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ በግብርና ኢንቨስትመንት መስኮች መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

የዩናይትድ ኪንግደም የግብርና ንግድ ልዑክ (UK Agribusiness Trade Mission) በኢትዮጵያ በግብርና የኢንቨስትመንት መስኮች የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ። የግብርና ሚኒስትር ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ ጫላ ሆርዶፋ(ዶ/ር) ከልዑኩ ጋር በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል። በመድረኩ በወተት ሀብት፣ በዶሮ፣ በማር፣ በእንስሳት ጤና፣ በዘርና በእንስሳት መኖ ልማት የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ምክክር ተደርጓል። ለልዑክ ቡድኑ በኢትዮጵያ ስላሉ የግብርናው የኢንቨስትመንት እድሎች…

Read More

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ የትብብር አድማሳቸውን በማስፋት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ፈረንሳይ የወዳጅነት ቡድን ዋና ሰብሳቢ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በፈረንሳይ ፓርላማ የአፍሪካ ቀንድ የወዳጅነት ቡድን ፕሬዝዳንት ሴናተር ሁግ ሳሪ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የሁለቱ ሀገራት የወዳጅነት ቡድን አባላት በፓርላማ ዲፕሎማሲ፣ በሕዝብ-ለሕዝብ ዲፕሎማሲና የምርጫ ስርዓትና አፈጻጸምን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ…

Read More

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ፈረንሳይ የወዳጅነት ቡድን ዋና ሰብሳቢ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በፈረንሳይ ፓርላማ የአፍሪካ ቀንድ የወዳጅነት ቡድን ፕሬዝዳንት ሴናተር ሁግ ሳሪ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የሁለቱ ሀገራት የወዳጅነት ቡድን አባላት በፓርላማ ዲፕሎማሲ፣ በሕዝብ-ለሕዝብ ዲፕሎማሲና የምርጫ ስርዓትና አፈጻጸምን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ…

Read More

ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት መከበር ሁሉም በተሰማራበት የሙያ መስክ ለአገሩ የሚጠበቅበትን ማበርከት አለበት

ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት መከበር ሁሉም በተሰማራበት የሙያ መስክ ለአገሩ የሚጠበቅበትን ማበርከት እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ። በሉዓላዊነት የተሰየመው ጳጉሜ-3 “ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ኃሳብ ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር የተከፈለን ዋጋ ክብር በመስጠት በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት ተክብሮ ውሏል። በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳው ዝግጅትም የፓናል ውይይትን ጨምሮ ለአገር ነፃነት የተከፈለን ውድ ዋጋ የሚያሳይ የአውደ-ርዕይ ዝግጅትና…

Read More

ኅብራችን ለሰላማችን – የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

ኅብረ ብዙ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለኅብር ቀን በሰላም አደረሳችሁ! ጳጉሜን 4 የኅብር ቀን “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ መልዕክት ተከብሮ ይውላል፡፡ በእርግጥም የኅብር ቀን ኢትዮጵያውያን ዓመቱን ሙሉ ልናከብረዉ የሚገባ ነው፤ ኅብራችን ብዙ ነውና፡፡ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በአመለካከት፣ በመልክዓ ምድር፣ በአመጋገብ፣ በአኗኗር ዘይቤ፣ በአለባበስ ወ.ዘ.ተ፡፡ ኅብራዊነታችን ሰፊ ነው፡፡ ይህ ኅብራችን ደግሞ ውበታችን፣ ሀብታችን፣ የደስታና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው፡፡…

Read More

በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ሂደት የሚከናወኑ ስራዎችን እንደግፋለን – የተመድ ድርጅቶች

በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ሂደት የሚከናወኑ ተግባራትን እንደሚደግፉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ተቋማት ገለጹ። የድርጅቶቹ ተወካዮች በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ስራዎችን መደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ ተገኝተዋል። የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) መንግስት…

Read More

በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም የ3 ጊዜ የሞት ፍርደኛ እንደነበር ፖሊስ አስታወቀ

ሰሞኑን በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ፣ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም 3 ጊዜ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት እንደነበር ፖሊስ ገልጿል፡፡ ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ እንደተቻለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታሕሳስ 25 ቀን 1999…

Read More

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢትዮጵያን ምርት የመግዛት ባህል ማዳበር ያሰፈልጋል፦ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢትዮጵያን ምርት የመግዛት ባህል ማዳበር ይገባል ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ ካዘጋጀው የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን ትኩረቱን የጥራት መሰረተ ልማት ላይ ያደረገ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት፤ ጥራት ለምርቶች…

Read More