Trendings

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመሯል፡፡ ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ቃለ ጉባዔውን መርምሮ በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ የቀጠለ መሆኑም ተመላክቷል። ምክር ቤቱ በጉባኤው ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው…

Read More

ፕሬዚዳንት ታዬ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን ገለጹ

በ2016 በጀት ዓመት በተለያዩ መስኮች ከ21 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ የፌዴራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ አቅርበዋል፡፡ በንግግራቸውም አጠቃላይ…

Read More

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል፡-

የምትሻገር ሀገር በማይሻገር ሐሳብ እየተናጠች ቆይታለች፣ የሚታረቅና የሚታረም የፖለቲካ ልዩነት እንደማይታረቅ ተደርጎ በመሠራቱ ሀገር በማይጠራ የፖለቲካ ሳንክ እንድትንገላታ ተገዳለች፣ የፖለቲካ ወለምታዎችን ለማቅናት ስብራቶችን ለመጠገን ስንጥቃቶችን ለመድፈን ስትል ዛሬም ለነገ የታሪክ የቤት ሥራ ለማስቀመጥ የሚደረጉት ሙከራዎች የሀገራችንን ፈተና አበርትተውታል፡፡ All reactions: 44

Read More

የሸካ ጥብቅ ደን – የብዝሃ ህይወት ስብጥር ተምሳሌት

የሸካ ተፈጥሮ ደን ህብረተሰቡ በሀገር በቀል ዕውቀቱ በባህላዊ መንገድ ጠብቆ ያቆየው የማህበረሰቡ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እሴት ውጤት ነው። ደኑ እስከ አሁን የብዝሃ ህይወት ስብጥሩን ሳይለቅ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ መምጣቱ ህብረተሰቡ ለተፈጥሮ ሀብት ያለውን ተቆርቋሪነት የሚያመላክት ነው። ሸካዎች የተፈጥሮ ደኑ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የመጠለያና የመዝናኛ ምንጭ እና መሠረትም ነው ብለው ያምናሉ። በተለያዩ የተፈጥሮ ፀጋዎች የታደለው የሸካ ምድር…

Read More

የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ነገ ይካሄዳል

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ- ሥርዓት ነገ ይካሄዳል። በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1 ዓመት ስራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ…

Read More

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊያንን የመከባበር ኃይል ያሳየ መድረክ ነው – የበዓሉ ታዳሚዎች

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊያን የአንድነትና የመከባበር ኃይል የሚያሳይ ትልቅ መሰባሰቢያ መድረክ ነው ሲሉ የበዓሉ ታዳሚዎች ገለጹ። በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በባህላዊ አልባሳት አጊጠው አዲስ አበባ የተገኙ በርካታ ሰዎች በሆራ ፊንፊኔ በመሰባሰብ የኢሬቻ በዓልን እያከበሩ ነው። ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጪ የሚመጡ እንግዶች በጋራ ተሰባስበው የሚገናኙበት ታላቅ ሁነት መሆኑን የሚናገሩት የበዓሉ ታዳሚዎች፤…

Read More

የሆራ ፊንፊኔ በዓል እሴቱን ጠብቆ የህዝብ ትስስርን፣ አንድነትንና የቱሪዝም እንቅስቃሴን ይበልጥ በሚያነቃቃ መልኩ በድምቀት ተከብሯል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ የህዝብ ትስስርን፣ አንድነትንና የቱሪዝም እንቅስቃሴን ይበልጥ በሚያነቃቃ መልኩ በድምቀት መከበሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ የተከበረውን የኢሬቻ በዓል አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ የህዝብ ትስስርና አንድነትን በሚያጠናክርና የቱሪዝም እንቅስቃሴን ይበልጥ በሚያነቃቃ መልኩ በድምቀት መከበሩን ተናግረዋል። በሆራ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ2017 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክልት አስተላለፉ

የተከበርከው የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ እንኳን አስቸጋሪውን የክረምት ወቅት አልፈህ ለብሩሁ ብራ ተሸጋገርክ! ኢሬቻ ዕርቅ ነው፤ ፈጣሪ ደግሞ ዕርቅ ይወዳል። የተጣሉ ሰዎች ቂም ይዘው ለኢሬቻ ወደ መልካ አብረው አይወርዱም። ኢሬቻ መትረፍረፍ ነው! ኢሬቻ ምስጋና ነው! ኢሬቻ ልምላሜ ነው! ለምለም ሣር ክብርን ፣ ፍቅርን እና መልካም ምኞትን ይወክላል። ብራ ሽግግር ነው፤ ያለፈውን ወደኋላ ትተን ወደ አዲስ ተስፋ…

Read More

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡርን ትርፋማ ተቋም ማድረግ በሚያስችል ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ተወያይተናል-ኢንጂነር ታከለ ኡማ

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡርን ትርፋማ ተቋም ማድረግ በሚያስችል የሶስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ። ኢንጂነር ታከለ፥ ለሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ በተደረገው ውይይት የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡርን የውስጥ አቅም ለማጠናከርም ከመግባባት ተደርሷል ብለዋል። በዚህም ተቋሙ ትርፋማ ለመሆን በሚያችለው የሶስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ‘በኤክስ’…

Read More

200 ሚሊየን የሕክምና ቴስት ኪቶችን በዓመት የሚያመርት የቻይና ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ላይ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

ጉዋንዥሁ ዎንዶ ባዮቴክ የተባለ 200 ሚሊየን የህክምና ቴስት ኪቶችን በዓመት የሚያመርት የቻይና ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብቶ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)÷ የጉዋንዥሁ ዎንዶ ባዮቴክ ኩባንያ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር)÷የፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ የሚገኝ ዘርፍ መሆኑን በመግለጽ ይህም ኩባንያው…

Read More