Trendings

የተሻለች ሀገር ለመገንባት ታዳጊ ሴቶች ላይ መስራት ይገባል – ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

የዘንድሮው አለም አቀፍ የታዳጊ ሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ “ታዳጊ ሴቶች ላይ መስራት የነገን የተሻለች ሀገር መገንባት ነው” በሚል መሪ መሪ ቃል በተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ታዳጊ ሴት ልጆች እየተጋፈጡት ያለውን ፈተና እንዲሻገሩ ለማስቻል በጋራ መረባረብና ትኩረት ሰጥተን መሰራት ይገባናል ብለዋል። ዛሬ ያልዘራነውን ነገ ማጨድ…

Read More

በጥቅምት ወር ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ለማስተናገድ ዝግጅት አድርጋለች – ሰላማዊት ካሳ

በጥቅምት ወር ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኮንፈረንሶችን ለማስተናገድ ዝግጅት ማድረጓን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ካለፈው ነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት በድምቅት መከበራቸውን አስታውሰዋል፡፡ በዓላቱ የሕዝቦችን ትስስር ከማጠናከር ባለፈ የአንድን ሀገር እምቅ ባህል እና እሴት…

Read More

ኢትዮ-ግሪን ሞቢሊቲ 2024 ዓለም አቀፍ ዓውደ ርዕይና ሲምፖዚየም ቅድመ ሁነት ተካሄደ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ኢትዮ- ግሪን ሞቢሊቲ 2024 በሚል ስያሜ በመጪዉ ህዳር ወር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ዓለም አቀፍ ዓውደ ርዕይና ሲምፖዚየም ያካሂዳል። የቅድመ ሁነት ፕሮግራሙ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የኢምባሲ ተወካዮች፣ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚሰሩ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የዘርፉ ባለሃብቶች እና ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ትናንት መሰከረም 28/2017 ዓ.ም አመሻሽ…

Read More

2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣ ዓመት ነበር፦ የምጣኔ ሀብት ባለሞያ

2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ ያመጣ ዓመት ነበር ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሞያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ገለፁ። በበጀት ዓመቱ 8.16 በመቶ የነበረውን አጠቃላይ ሀገራዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት በቀጣይ ወደ 8.4 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱንም ባለሞያው በተለይ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል። በወጪ ንግድ ዘርፍም ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ጠቅሰዋል።…

Read More

ባለፉት 6 ዓመታት 11 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታገጠም መልማቱ ተገለፀ

ባለፉት 6 ዓመታት 11 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታገጠም መልማቱን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዝላታን ሚሊሲክ ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ ለዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ የግብርና ስራን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ግብርና የኢትዮጵያን አንድ ሶስተኛ አጠቃላይ እድገት፣ ሁለት ሶስተኛውን ኤክስፖርት እንዲሁም 65 በመቶ የገቢ ምንጭ እንደሚሸፍን አመልክተዋል። 25…

Read More

ኢትዮጵያ በተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ለ3ኛ ጊዜ አባል ሆና ተመረጠች

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ከ2025-2027 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሦስተኛ ጊዜ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች፡፡ ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ዙር የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል በመሆን የተመረጠቸው በ79ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ነው፡፡ ቀደም ሲል በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2015 እና ከ2016 እስከ 2018 ባለው ጊዜ ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ አባል በመሆን ማገልገሏ ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ለሦስትኛ…

Read More

መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ተደረገ

መንግሥት ከፍ ያለውን ድጎማ የሚያደርግበት ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የነዳጅ ሪፎርም አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ እና የቀጣይ አቅጣጫ አስመልክቶ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አማካሪ አህመድ ቱሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ የሪፎርም ሥራ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ጥሩ የሚባል ውጤት ማምጣቱን አንስተዋል። የሪፎርሙ…

Read More

ኮሚሽኑና የሐይማኖት ተቋማት በጋራ ለመሥራት ግብረ-ኃይል አዋቀሩ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና የሐይማኖት ተቋማት በቀጣይ በጋራ በሚሠሯቸው ተግባራት ላይ ግብረ-ኃይል በማቋቋም በትብብር ለመስራት ተስማሙ፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሐይማኖት ተቋማትን ሚና እና ተሳትፎ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ለማጎልበት ያለመ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት እና በጉባዔው በአባልነት ያልተመዘገቡ የሐይማኖት ተቋማት መሳተፋቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡ የኮሚሽኑ ዋና…

Read More

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መልካም ምኞታቸውን ገለጹ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ከፍተኛ አመራሮች ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሰራተኞች ለፕሬዚዳንቱ መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸውም ምኞታቸውን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Read More

የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎች የህዝቦችን ወንድማማችነት በሚያጠናክር መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ተገለፀ

የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎች የህዝቦችን ወንድማማችነት በሚያጠናክርና ዘላቂ ሰላምን ሊያሰፍን በሚችል መልኩ እልባት ለመስጠት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በስብሰባው፤ የማንነት አስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው 2017 በጀት ዓመት እቅድ፤ የወልቃይት፣ ራያና ጠለምት ጥያቄዎችን ለመመለስ ከአካባቢው መስተዳድርና ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማካሄድ በአካባቢው ያለውን…

Read More