በ2017 በጀት ዓመት በማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘርፎች ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ተናገሩ ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ ተጀምሯል ፡፡ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወንድሙ ኩርታ በጉባኤው መክፈቻ እንደተናገሩት ባለፉት የበጀት ዓመት ምክርቤቱ በህገ መንግስቱ የተሰጠዉን ሀላፊነት ለመወጣት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል። ምክር ቤቱ በህገ-መንግስትና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ የተሰጠዉን ተግባርና በበጀት…
