የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በነበረው የሁለተኛ ቀን ውሎው የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል።
የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በአቶ ቆጭቶ ገብረማርያም ቀርቧል። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም ለምክርቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ፍርድ ቤቶች ነጻና ገለልተኛ ሆነዉ የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸው ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙም ገልጸዋል። በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ ፍርድቤቶች የተሰጣቸውን ህግ የመተርጎም ስልጣንን…
