ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያንን ያስተሳሰረ ትውልድ ተሻጋሪ ብርሃን ነው ሲሉ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ ገለጹ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በህብረት የተሳካ የኢትዮጵያ የማንሰራራት መገለጫ የይቻላል ማሳያም ጭምር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ በብዙ ልፋትና መስዋዕትነት የተገነባው ታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ በመስከረም ወር እንደሚመረቅ ማብሰራቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የጋራ ተጠቃሚነት አቋሟ የጸና መሆኑን መናገራቸውም እንዲሁ። ኢዜአ በታላቁ…
