Trendings

የኮሪደር ልማት ስራን የተረዱትና የተገበሩት ሞዴል አርሶ አደር አቶ አመነ አምበሎ!

በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ የካንጋ ቀበሌ ሞዴል አርሶ-አደር አቶ አመነ አምበሎ ቤታቸውን እና ግቢያቸውን ውብ፣ ጽዱና ለመኖር ምቹ ማድረግ ከአባቶች የወረሱት ባህል ቢሆንም ፤ አሁን መንግስት በሰጠው ትኩረት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። የቀለም ትምህርትን እስከ ሰባተኛ ክፍል እንደተማሩ የሚናገሩት ሞዴል አርሶ-አደሩ ፤ ስድስት ልጆችን በማስተማር ለውጤት ማብቃታቸውን ተናግረዋል። ባላቸው ዕውቀትና ትጋት ጽዱና ምቹ አካባቢን ከመፍጠር በላይ…

Read More

በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በክልሉ መጠነ ሰፊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል። አቶ ፍቅሬ አማን

በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅ/ጽ/ቤት የ2017 ዓ/ም የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በአማያ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የአፈፃፀም ግምገማ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በክልሉ መጠነ ሰፊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ፍቅሬ፥ ፓርቲው በክልሉ የህዝቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና…

Read More

4 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የተመደበለት የታርጫ ጪዳ ሎት 3 አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ።

የመንገድ ፕሮጀክቱ 64.8 ኪሎሜትር ርዝመት እንዳለውም ተገልጿል ። የታርጫ ጪዳ መንገድ ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል። ይህንን ፕሮጀክት ዳግም መጀመሩን በማስመልከትም ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የመንገድ ፕሮጀክቱ ተጀምሮ መቋረጡ የአካባቢውን ህብረተሰብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮችን በእጅጉ የጎዳ መሆኑን አስታውሰዋል። የብልጽግና ፓርቲ እና መንግስት ይህንን የህዝቡን የመልካም…

Read More

የሥራና ክህሎት ቢሮ ”ብሩህ አዕምሮዎች፤በክህሎት የበቁ ዜጎች በሚል መሪ ቃል የክህሎት፤ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድርና ኤግዚቢሽን ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነዉ።

በውድድርና ኤግዚቢሽን መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ እንደገለጹት፤ በፊት ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚሰጠዉ ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ በዘርፉ ውጤት ተገቢዉ ዉጤት ሳይመዘገብ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም የተጀመሩ የተቋማት ግንባታዎች ተጠናቅቀዉ አገልግሎት ባለመስጠታቸውና ተቋማት በሚፈልገው ልክ ቴክኖሎጂ ከማሸጋገር አንጻር የነበራቸው ውስንነቶች ተግዳሮት እንደነበርም አስታውሰዋል። ዋና አፈ-ጉባኤው…

Read More

የዲሪ ማሻ አስፋልት መንገድ ግንባታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችንን ይፈታል – የአካባቢው ነዋሪዎች

የዲሪ ማሻ አስፋልት መንገድ ግንባታ ዳግም መጀመሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እንደሚፈታላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። የፌደራልና የክልል አመራሮች በተገኙበት ተቋረጦ የነበረው የዲሪ ማሻ አስፋልት መንገድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሥራ ትናንት ተጀምሯል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ2010 ዓ.ም ግንባታው ተጀምሮ በሥራ ተቋራጭ አቅም ማነስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የዲሪ ማሻ አስፋልት መንገድ ዳግም ሥራ መጀመሩ የአካባቢውን ህብረተሰብ…

Read More

በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ውጤታማ መሆናቸውን የታርጫ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ ።

በታርጫ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ያሉ የልማት ስራዎችን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ወጣቶቹ በተሰማሩባቸው የእንቁላል ጣይ ዶሮ በቀን ከ450 በላይ እንቁላል እያገኙ መሆናቸውን ለርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዷ በሆነችሁ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። የሌማት ትሩፋት አካል የሆነው የእንቁላል ጣይ…

Read More

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው፦ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 3ኛ ዙር 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ የተከበሩ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ መቱ አኩ ጉባኤው ያለፉትን የ9 ወራት አፈፃፀም በመገምገም ለቀጣይ በቂ ግብአት የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀው ምክር ቤቱ ህገ መንግሥታዊ ተልዕኮውን አንግቦ የክልሉን ህዝብ መብትና ጥቅም በማስከበር ረገድ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ…

Read More

ለአመታት ተቋርጦ የነበረው የዲሪ ማሻ አስፋልት መንገድ ስራ እንደገና ሊጀመር ነው ።

ለአመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የሰነበተው የዲሪ_ማሻ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ እንደገና ወደ ስራ የማስገባት ስነስርዓት በካፋ ዞን ጊንቦ ወረዳ ይደረጋል። ይህንን ስነ _ስርዓት ለማስጀመር የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ አየለ የተገኙ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አቀባበል አድርገውላቸዋል።…

Read More

የወጣቶች ክንፍ የ2017 ዓ.ም.የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ሰዒድ ኢብራሂም ባደረገው ንግግር፣በኢኮኖሚ ዘርፍ ወጣቶች ቁጠባን ባህል አድርገው ውጤታማ በሚሆኑባቸው ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ የተሻለ እንቅስቃሴ መደረጉን ገልጿል ። ወጣቶች የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት መደረጉን ጠቅሰው በተለይ ወጣቱን ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማስገባት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በማመቻቸት ላይ እንገኛለን…

Read More

በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 227 ሄክታር ማልማት የሚችሉ 11 የመስኖ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑ ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት አፈፃፀም ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የተናገሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተርኢንጂነር አሸናፊ ሽብሬ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አክለዋል። በክልሉ መንግሥት በጀትና ዘርፉን በሚደግፉ በተለያዩ ፕሮግራሞች የበጀት ድጋፍ በርካታ የመስኖ ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንዳለ…

Read More