በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ በተከሰተው የአባ ሳንጋ በሽታ ህብረተሰቡ ላልተወሰነ ጊዜ በዞኑ ውስጥ ጥሬ ስጋ መመገብ እንደማይገባቸው የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ
በምዕራብ ኦሞ ዞን በሱሪ ወረዳ በኮካ ቀበሌ የተከሰተው የአባ ሳንጋ በሽታ የመከላከል ሥራዎች ላይ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ። የዞኑ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሼማጂ ጉሪጭማ እንደተናገሩት በዞኑ በሱሪ ወረዳ በአባ ሳንጋ በሽታ የሞተ ሰው አለመኖሩን ያስታወቁት ኃላፊው በዞኑ አርብቶ አደር መምሪያ ኃላፊ አማካይነት ሰባት ሰዎች በአባ ሰንጋ በሽታ ሞቱ ተብሎ ለDW የተሰጠዉ መረጃ ስህተት፣ ያልተገመገመና በዞኑ…
