Trendings

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት የክልሉ የአስተዳደር ጉዳዮች ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ የአስተዳደር ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ይገኛል። በግምገማዉ መድረኩ እንደክልል በሩብ ዓመቱ ታቅደው በጥንካሬ የተከናወኑ ተግባራት እንዲጠናከርና ድክመቶችን በጋራ በመገምገም እንዲሁም ቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል። የክልሉ የአስተዳደር ተቋማት ማለትም ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፣…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመሠረተ ልማት ክላስተር ተቋማት የ9 ወራት የተግባር አፈፃፀም ግምገማ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዋ ሳፒ እንደገለፁት እያደገ የመጣውን የህዝብ የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት የጋራ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይገባል ብለዋል ። በመሰረተ ልማት ክላስተር ሥር ያሉ ተቋማት በዕቅድ አፈፃፀም ያለውን ጥንካሬና ጉድለቶች በመለየት የጋራ አረዳድ በመያዝ ለቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም መዘጋጀት…

Read More

በኮንታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት “የአስተሳሰብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በዞን ማዕከል ዞናዊ የአመራር አቅም ግንባታ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ሀገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታ የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ በ2 ቡድን ውይይት የሚደረግ ሲሆን አመራሩ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ራሱን እንዲያዘጋጅ ለማስቻል ያለመ ስለመሆኑ ተመላክቷል። በመድረኩ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙን ጨምሮ የዞን አመራሮች፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Read More

ዞናዊ ነበራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ አጠቃላይ የዞን አመራርና ወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ አጠቃላይ የዞን አመራርና የወረዳ እና ከተማ አስዳደር አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፥ የመድረኩ ዓላማ ቀደም ሲል በተሰጡ የአመራር መድረኮች የተገኙ አቅሞችን በማቀናጀትና በአመራር መካከል የተግባር አንድነትን በመፍጠር የህዝብ የልማት አቅሞችን…

Read More

የውስጥ ጥንካሬ እና አቅም ለውጭ ግንኙነት ስኬታማነት ፋይዳዉ የላቀ ነው፦የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የውስጥ ጥንካሬ እና ዐቅም ለውጭ ግንኙነት ስኬታማነት ፋይዳዉ የላቀ በመሆኑ በዚህ ላይ አተኩሮ መሥራት እንደሚገባ የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ፡፡ “ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለኢትዮጵያ መንሰራራት” በሚል መሪ መልዕክት ለኮሙኒኬሽን ዘርፉ የክልል እና ከተማ አስተዳደር መዋቅር አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በአዲስአበባ እየተሰጠ ያለው ሥልጠና በሁለተኛ ቀን ውሎዉ ጂኦ-ፖለቲካዊ ዓውዶች እና የውጭ…

Read More

ሪፖርታዥ

የክልላችን የበልግ ስራ እንቅስቃሴ በሀገራችን ታርክ የግብርናው ዘርፍ በኢኮኖሚው ለረጅም ዓመታት ብቻውን የመሪነት ሚና ሲጫወት መቆየቱና አሁንም ትኩረት ከተሰጣቸው የብዝሀ ኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብዙ ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ነው። ከነዚህም አንዱና ጉልህ ሚና ያለው የክልሉ ግብርና እና የተፈጥሮ ዘርፍ ነው። የክልል ግብርና ቢሮው የተፈጥሮ ሀብት እንዳይጎዳ በመጠበቅ፣…

Read More

የደቡብ ሞዕራብ ኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ያዘጋጀው የምርምር ስራዎች ኢግዚቢሽን ተከፈተ

በተቋሙ እስካሁን 218 ቴክኖሎጂዎችና እና መረጃዎችን በሰብል፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በእንስሳት እርባታ ማላመድና ማፍለቅ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 123 ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር ለተጠቃሚ አርሶና አርብቶ አደሮች ማድረስ መቻሉን ተነግሯል። ኢንስቲትዩት በቦንጋ ከተማ ባዘጋጀው አመታዊ የምርምር ስራዎች ኮንፈረንስ ላይ በሰብል፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በእንስሳት እርባታ ዘርፍ የተሰሩ የምርምር ውጤት ኢግዚቢሽን ለዕይታ አብቅቷል። የኮንፈረንሱ ታዳሚዎች በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች…

Read More

ኢንስቲትዩቱ 123 ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር ለተጠቃሚ አርሶና አርብቶ አደሮች ማድረስ ተችሏል።

የደቡብ ሞዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የምርሞር ኮንፈረንስ ግምገማ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ትኩረት ከተሰጣቸው የኢኮኖሚ መሠረቶች አንዱ የግብርና ክፍሌ ኢኮኖሚ መሆኑን የገለጹት የክልሉ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ ኢንስቲትዩቱ ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሰራ ያለው አበረታች ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል። የክልሉን የግብርና እምቅ አቅም በተገቢው…

Read More

የንጹህ መጠጥ ውሃ በማግኘት መደሰታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ የጌጫ ከተማና ጋቲባ ቀበሌ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አግልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ያነጋገርናቸው የጌጫ ከተማና ጋቲባ ቀበሌ ነዋሪዎች በወረዳው የንጹህ መጠጥ ውሃ ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። በጌጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ የነዋሪዎች ረጅም ዓመታት ጥያቄ ከመሆኑም በላይ ንጽህና ያልጠቀውን ውሃ ከተለያዩ ምንጮች በመጠቀማቸው ራሳቸውንና የቤተሰብ አባሎቻቸው በተለያዩ…

Read More

#ካንካርና_ኩችጓ

ባህል የአንድ ብሔረሰብ ማንነት መገለጫው፤ ትልቅ እሴቱ ነው። ባህልን ማልማት፣ ማሳደግ ለትውልድ ማሸጋገር ደግሞ የአሁኑ ትውልድ ትልቅ አደራው ነው። ይህ ትልቅ አደራ ሳይሸረፍ፣ሳይበረዝ የጥንት ይዘቱን ጠብቆ እንዲለማ ማድረግም ያስፈልጋል። በክልላችን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔረሰቦች አንዱ የፃራ ብሔረሰብ ነው ። ብሔረሰቡ የራሱ የሆኑ ባህላዊ እሴቶች አሉት ።ከእነዚህ እሴቶች ውስጥ አንዱ ባህላዊ አለባበስና አጋጌጥ ተጠቃሽ ነው…

Read More