የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ የገጠርና ከተማ ዕድገት ማመጣጠን እንደሚገባ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ በልዩ ልዩ የኢንዱስትሪ ስትራቴጅዎችና ፖሊሲዎች ፤በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን እና ዲጂታላይዜሽን ላይ ለካፋ ዞን የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ የገጠርና ከተማ ዕድገት ማመጣጠን እንደሚገባ የገለጹት የቢሮው ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ ስልጠናው የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች የመንግሥት ዓላማና ተልዕኮ ለመፈጸም ግንዛቤ የሚያሳድግ እንደሆነ ተናግረዋል።…
