በሸካ ዞን ግብርናን ለማዘመን የሚያስችሉ የ117 ሚሊዮን ብር የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ መሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉና ከ117 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። በክልሉ የግብርና ቢሮ በምግብ ስርዓተ ማጠናከሪያ ፕሮግራም ድጋፍ የሚገነቡትን የእነዚህን ፕሮጀክቶች መሠረተ ድንጋይ ያስቀመጡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ናቸው። በዞኑ ያለውን እምቅ የግብርና አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ…

Read More

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ፣ ሁሉም ፓርቲዎች ለምርጫው ስኬት በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ተጠየቀ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውይይት በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በጋራ ምክር ቤቱ የውይይት መድረክ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፤ በክልሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ግንባታ ላይ በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል። መጪው ምርጫ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና የሀገረ መንግስት ግንባታው…

Read More

በዳውሮ ዞን የሎማ ቦሳ ወረዳና የገሳ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በሰልፍ እየገለጹ ነው

​በዳውሮ ዞን የሎማ ቦሳ ወረዳ እና የገሳ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች የብልጽግና ፓርቲን ዓላማና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን በመደገፍ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ማካሄድ ጀምረዋል። ​ዛሬ ረፋዱን በገሳ ከተማ በተጀመረው በዚህ ሰልፍ ላይ የየአካባቢው ነዋሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች በነቂስ ወጥተው ድጋፋቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ሰልፈኞቹ የፓርቲውን ዓላማ የሚደግፉና የመንግሥትን የለውጥ ጉዞ የሚያበረታቱ ልዩ ልዩ መፈክሮችን እያስተጋቡ ነው።…

Read More

ምርጫ የህዝብ ፍላጎት የሚገለጽበት ከፍተኛ ሀገራዊ ሂደት በመሆኑ ሁሉም አካላት በህግ መሠረት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አስታወቀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስነ-ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን በምርጫ ስነምግባር እና በሀብት ምዝገባ ዙሪያ ለስር መዋቅሮች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ እንደገለጹት፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ የምርጫ ሥነ_ምግባር መመሪያን በጥልቀት በመረዳት ለመተግበር የሚያስችል አቅም ለመገንባት ያለመ ነው። 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በክልላችንና በፌዴራል ደረጃ የሚካሄድ ትልቅ ሀገራዊ ሂዳት ነው ያሉት ኮሚሽነር…

Read More

የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶቹ የህዝብን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተፎካካሪ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት አባላት በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮርደር ልማት እና የመሰቦ አንድ ማዕከልን ጎብኝተዋል። የልማት ፕሮጀክቶችን በስፍራው ተገኝተው የተመለከቱ የጋራ ምክር ቤቱ አባላት ፤ እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። እንደ አባላቱ ገለጻ፣ መሰል የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው የዴሞክራሲ ስርዓቱን በጽኑ…

Read More

ጉባኤው በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የጋራ ድምጽ ማሰማት የሚቻልበትን ዕድል ማመቻቸት ነው

የአፍሪካ ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ (ASMIS) ዋነኛ ዓላማም በተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የጋራ ድምጽ ማሰማት የሚችሉበትን ዕድል ማመቻቸት እንደሆነ የፐልስ ኦፍ አፍሪካ አስተባባሪ አቶ በረከት ሲሳይ ገለጹ። የአፍሪካውያንን አጀንዳ ለማስረፅና የጋራ ድምፅን ለማሰማት ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አክለዋል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከ ኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር…

Read More

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለጠንካራ ሀገር ግንባታ እያደረጉ ያለውን አስተዎጽኦ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በቤንች ሸኮ ዞን እየተሰሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት በገበታ ትውልድ መርሃ ግብር የተመረቀው የደንቢ ኢኮ ሎጅን፣ የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ፣የደቡብ ምዕራብ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የስራ እንቅስቃሴውን ተዘዋውረው ተመልክዋል። የምክር ቤቱ አባላት በየአከባቢው እየተከናወኑ…

Read More

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የአገሪቱን ዘላቂ ዕድገትና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ማዕከል ባደረገ መልኩ እየተገነባ ነው

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የአገሪቱን ዘላቂ ዕድገትና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ማዕከል ባደረገ መልኩ እየተገነባ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካለፈው ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን ድረስ የሚቆየውን የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ በይፋ መክፈታቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ በዘንድሮው “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ላይ የሀገራዊ ርዕያችንን ተጨባጭ ስኬት መመልከት…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት የአፈጻጸም ክፍተቶች እንዲታረሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት፣ የማረሚያ ተቋም እና የቦንጋ ዘመናዊ መናኸሪያ የግንባታ ሂደትን በዛሬው ዕለት ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በክልሉ መንግሥት በከፍተኛ በጀት ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የቦንጋ መናኸሪያ የመጀመሪያው ምዕራፍ የአስፋልት ንጣፍ ሥራ አሁን ላይ እየተገባደደ ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል። ርዕሰ…

Read More

የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል፦የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት

የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጹ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሚዛን አማን ከተማ የተለዬዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። የጋራ ምክር ቤቱ በቤንች ሸኮ ዞን የህዝብን ሁሉአቀፍ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል። የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ፣የደቡብ ምዕራብ መሶብ…

Read More