በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የታርጫ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት በመሆኑ መደሰታቸውን የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በበኩላቸው መናኸሪያው ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ንብረት ውጭ በሚያድርበት ወቅት ካለው ስጋት ነፃ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች አቶ ወ/ማርያም ብትሬ እና ወ/ሮ አባይነሽ ሳና ቀደም ሲል የታርጫ ከተማ መናኸራያ የመንገደኞች ማረፍያ፣ ካፍቴሪያ፣ የትኬት መቁረጫ ቢሮና መኪና ማቆሚያ ቦታ ምቹ ያለመሆኑን አንስተው አሁን ግን ዘመናዊ መናኸሪያ ተገንቢቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል። በግንባታ ምክንያት…
