በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ 7ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ የምርጫ አስመልክቶ የቅስቀሳ እና የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ስርዓት በወለደው ጭቁን አስተዳደር በወለዳቸው በተለያዩ ችግሮች ተቀፍድዳ በመያዝ ድህነት ውስጥ የነበረች ሀገር ስለመሆኗ አስረድተው እነኚህ ችግሮች አንገብግበው የተወለደው ብልፅግና ፓርቲ ፈተናዎችን ወደ ዕድልና ድል በመቀየር በፍትሐዊነት ሁሉአቀፍ ዕድገት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በቀጣይ ጊዜያት በአፍሪካ ብሎም…
