ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ከ353 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው ሆስፒታል የመሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ፣ የያዶታ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል። ከ353 ሚሊዮን በላይ በሆነ የክልሉ መንግሥት የበጀት የሚገነባው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአግልግሎት ክፍት እንደሚኾን ተመላክቷል። የሆስፒታሉ መገንባት ከዚህ ቀደም በአከባቢው ከጤና ተቋማት ተደራሽነትና ጥራት ጋር ተያይዞ…
