በራሳቸው ፋብሪካ እሴት ጨምሮ በመሸጥ ከሌሎች ጥገኝነት ለመላቀቅ እንደሚሰሩ በካፋ ዞን በሻይ ልማት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ገለጹ።
አርሶ አደሮቹ በአሁኑ ሰዓት ያመረቱትን ሻይ ለውሽውሽ ሻይ ልማት ድርጅት እያቀረቡ መሆኑንም ጠቁመዋል። በዞኑ ጊምቦ ወረዳ ምቺቲ ቀበሌ በ1997 ዓመተ ምህረት በ6 አርሶአደሮችና በ6 ሄክታር ማሳ ላይ የተጀመረው የሻይ ልማት ዛሬ አድማሱን አስፍቶ በወረዳው 6 ቀበሌዎችን ከማዳረሱም በላይ በርካታ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ምርት መስጠት ባቆመ አሲዳማ መሬት ሊይ በመተከል ውጤት መስጠት የሚችል ከመሆኑም…
