በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በከተማዋ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የማሻ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ገለፁ።
ባለፉት አምስት አመታት በፓርቲው መሪነት በከተማዋ የተሰሩ ጠንካራ ስራዎችን ለማስቀጠል እንዲሁም 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን የሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የውይይት መድረክ በማሻ ከተማ ተካሂደዋል ። በውይይት መድረኩ ላይ መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አንዷለም ጌታቸው በከተማዋ ባለፋት የአምስት አመታት በርካታ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው በዚህም የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እንዲሁም የሆስፒታል ግንባታ…
