ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ውጤታማ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ተቋም መገንባት ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለፀ
“የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ የውይይት መድረክ በማሻ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በመክፈቻ ንግግራቸው ሚዲያ በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚዊና በማህበራዊ ዘርፎች ውጤታማ ለውጥ እንዲመዘገብ እንዲሁም አካባቢን በማስተዋወቅና መላው ህዝብ የልማት…
