ከካፋ ዞን የተወጣጡ መምህራን በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
ከአውራዳ፣ ከሺሺንዳና ከዋቻ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከጨናና ከሺሾ-እንዴ ወረዳዎች የተወጣጡ መምህራንና የማህበራዊ ክላስተር አስባባሪዎች የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ እየተከናወነ የሚገኘውን የሁለተኛ ምዕራፍ ኮሪደር ልማትን በተመለከተ የቦንጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ፤ የአከባቢው ነዋሪዎችም እያደረጉት ያለውን ድጋፍ ማብራራታቸዉን ቦንጋ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
