ከተሞች ለነዋሪዎች የተመቹ እንዲሆኑ የተጀመሩ ጥረቶች ለውጥ እያመጡ መሆናቸውን የደካ እና ጀሙ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ገለጹ
ደካ እና ጀሙ ከተማ አስተዳደሮች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት በካፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ከሚገኙ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ሁለቱ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በ2013 ዓ.ም በፈርጅ ሶስት የታቀፉ ከተሞች ሲሆኑ እነዚህን ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ሰፊ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። የደካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በላይ ባደገ እንደገለጹት፤ ደካ ከተማን ለነዋሪዎች ለመኖሪያ…
