ዓድዋ የህብረትና የአንድነት ምልክት መሆኑ ተገለፀ
በኮንታ ዞን 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። የዕለቱን መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አማካሪ አቶ ብርሃኑ ተፈሪ ድሉ ከኢትዮጵያዊያን የወል ታሪኮች መካከል ታላቁ ታሪክና ግዝፈቱም የዓለምን የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ የሰበረ፣ የፀረ-ቅኝ ትግል አቅጣጫን የጠቆመና የታሪክ ቢያኔ የቀየረ ሀቅ ነው ስሉ ተናግረዋል። አቶ ብርሃኑ የአባቶቻችንን…
