ክልሉ በምግብ ዋስትና መርሀ ግብር የታቀፉ ወገኖችን ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር እየሰራ ነው
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምግብ ዋስትና መርሀ ግብር የታቀፉ ወገኖችን ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ለአደጋ የማይበገር ማህበረሰብ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ለማ መሠለ(ዶ/ር) እንዳሉት በክልሉ በምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የታቀፉ ወገኖችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር እየተሰራ ነው። በዚህም ለአደጋ የማይበገር ማህበረሰብ ለመፍጠር የመካከለኛ ጊዜ ስትራቴጂ ዕቅድ ተቀርጾ እየተሰራ…
