አርጀንቲና ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ የመሥራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች
አርጀንቲና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር በማሳደግ በትምህርት ዘርፍ በጋራ የመሥራት ፍላጎት እንዳላት አስታውቃለች፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ የአርጀንቲና አምባሳደር ኢግናሲዮ ሮካታግሊታ ጋር በትምህርት ዘርፉ በትብብር በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም ሀገራቱ በሚኖራቸው ትብብር በትምህርት ዘርፍ ሊሠሩባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋርም በትብብር መሥራት የሚቻልበት ምቹ ሁኔታ አለ ማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡…
