በፓርቲያችን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንዲሳኩ አመራሩና አባሉ በቁርጠኝነት መስራት ይገባቸዋል፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ”ከቃል እስከ ባህል”በሚል መሪ ቃል በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው። ውይይቱ በጉባዔው በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ትግበራ ለመግባት ዓላማ ያደረገ ነው። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ብልጽግና…
