የተሻለ ተቋማዊ አደረጃጀትን መፍጠር ለጠንካራ አገረ መንግሥት ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ በመሆኑ በተቀናጀ ርብርብ ሊሠራ እንደሚገባ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችና አባለት ገለጹ
በክልሉ ታርጫ ማዕከል የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት ከቃል እስከ ባህል በሚል መርህ ሃሳብ መነሻ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና በተቀመጠው አቅጣጫ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ የተሳተፉ የታርጫ ማዕከል የክልል ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ተግባራቸውን ለማከናወን ተቀናጅተው እንደሚሠሩም አስረድተዋል። የታርጫ ማዕከል የክልል ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ…
