የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ፍጹም የበላይነት ተጠናቀቀ
በዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ ያለው የዱባይ ማራቶን ዛሬ ሲከናወን በወንዶች አትሌት ቡቴ ገመቹ፤ በሴቶች ደግሞ አትሌት በዳንቱ ሂርጳ አሸንፈዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን የሮጠው አትሌት ቡቴ ገመቹ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2፡04፡50 የሆነ ጊዜ ፈጅቶበታል፡፡ አትሌት ቡቴ የ80 ሺህ የአሜሪካን ዶላርም ተሸላሚ ሆኗል፡፡ አስቀድሞ በግማሽ ማራቶኖች ይሳተፍ የነበረው ቡቴ የዱባይ ማራቶንን በማሸነፉ መደሰቱን ተናግሯል፡፡ የመጀመሪያውን 36 ኪሎ ሜትር…
የኢትዮጵያና የቻይና 55ኛ የወዳጅነት በዓል እየተከበረ ነው
የኢትዮጵያ እና የቻይና 55ኛ የወዳጅነት በዓል በወዳጅነት አደባባይ እየተከበረ ነው፡፡ በመርሐ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በመድረኩ÷የ55ኛ የወዳጅነት ክብረ በዓል በሁሉም መስኮች እየተጠናከረ ለመጣው የኢትዮጵያ እና የቻይና የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳያ ነው ብለዋል።…
“ቢስት ባር” በቤንች ብሔር ዘንድ የአዲስ ዓመት ብስራት ነዉ:- ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)
የደቡብ ምዕራብኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የክልላችን ህዝቦች ቱባ የታሪክና የባህል እሴቶች ያሏቸው እንደ አንድ ቤተሰብ በባህላቸውና ትውፊታቸው የተሳሰሩ የውብና ማራኪ ባህሎች ባለቤቶች ናቸው ብለዋል። በክልላችን ከሚገኙ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል አንዱ የቤንች…
ሕዝቡ ለቢስት ባር በዓል አካባበር የሚያደርገዉ ንቅናቄና ተነሳሽነት አስደሳች ከመሆኑ ባሻገር የቤንች ብሔር ባህል ሳይበረዝ ተጠብቆ እንዲቆይ የወጣቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ገለጹ፡፡
ምሁራኑም የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል ቢስት ባር ለሀገራችን ቱሪዝም ዕድገት የጎላ ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል፡፡ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የ2024 የማንዴላ ዋሽግተን ፎሎዉ አሸናፊ ረዳት ፕሮፌሰር ታገል ወንድሙ እንዳስረዱት የቤንች ሕዝብ የራሱ የሆነ ማንነት ፣ ለየት ያለ የዳኝነት ሥነ-ሥርዓት ፣ የአመጋገብና የአለባበስ ሥርዓት ያለዉ ሁሉን አቃፊ ሕዝብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ብሔረሰቡ በዱም ሥርዓት የሚተዳደር…
ቢስት ባር ወንድማማችነት እና የአብሮነት ጎልቶ የሚታይበት የቤንች ብሔር ታሪካዊና ባህላዊ ዕሴት አንዱና ዋነኛ ማሳያ ነው አሉ የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች።
ለቤንች ብሄር ዘመን መለወጫ (ቢስት ባር ) የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ ይገኛል። የፊታችን ሰኞ ጀምሮ በድምቀት ለሚከበረው የቤንች ብሄር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል (ቢስት ባር) የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በሚዛን አማን ከተማ እና በዓሉ በሚከበርበት የአማን የቀድሞ አየር ማረፊያ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል። የበዓሉን ዝግጀት ለማሳለጥ የተቋቋመው ኮሚቴ የህብረተሰብ ተሳትፎ በማጠናከር ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የሚገልጹት…
የብሔራዊ ቤተ መንግሥት ዕድሳት ተደብቆ የቆየውን የኢትዮጵያ የዳበረ የዲፕሎማሲ ታሪክ ለዓለም ያሳየ ነው-አምባሳደር ብርቱካን አያኖ
የብሔራዊ ቤተ መንግሥት ዕድሳት ተደብቆ የቆየውን የኢትዮጵያ የዳበረ የዲፕሎማሲ ታሪክ ለዓለም ገልጦ ያሳየ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ፡፡ የብሔራዊ ቤተ መንግሥት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቅርብ ክትትል ደረጃውን ጠብቆ ታድሶ ለምርቃት በቅቷል፡፡ ዕድሳቱ የኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክና ገናና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ደምቀው እንዲታዩ አድርጓል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ…
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የካድፕ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በመሪዎች ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካድፕ) አስቸኳይ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። በስብሰባው ላይ የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፤ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት ጨምሮ የህብረቱ አመራሮች፣ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የግብርና ሚኒስትሮች፣ የልማት አጋሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፥ በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት…
