ብልጽግና ትናንትን እያከመ ነገን በመተለም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እንዲትሸጋገር በቁርጠኝነት እየሰራ ፓያለ ፓርቲ ነዉ፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና ምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። በመረሐ-ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንደተናገሩት፤ የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የተጋረጡ ውስብስብ ችግሮችን እየጠገነ አስደናቂ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል። የኢኮኖሚ ልዕልና ለማረጋገጥ እንዲሁም የተዛባ መዋቅራዊ ችግር ለማረም፣ በሀገር ኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያ ፣…
