የብልጽግና ጉዞውን ዕውን ለማድረግ የሲቭል ሰርቪስ ሪፎርም በተቀመጠው አሠራር ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የፋይናንስና ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ላይ ለአመራርና ባለሙያዎች ስልጠና በቦንጋ እየሰጠ ይገኛል። በስልጠናው መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊና ፊዝካል ፖሊሲና መንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ አቶ መለሠ ኡሮ የብልጽግና ጉዞውን ዕውን ለማድረግ በሀገር ደረጃ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን ገልጸዋል። ለዚህም ስኬታማነት…
