በገቢ ተቋማት የሚታዩ የሥነ-ምግባርና የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችን በመቅረፍ ለውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት አዘጋጅነት የገቢ ተቋም ፈፃሚዎች አገልግሎት አሰጣጥና ሥነ ምግባር ችግሮችን ለመፍታት ከንግድ ማህበረሰብ ጋር የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ አካሂዷል። የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በላይ በወቅቱ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ቴፒ ከተማ የራሱን የወጪ ፍላጎት በራሱ ገቢ መሸፈን የቻለ ቢሆንም ፣ ያለውን አቅም ሙሉ በሙሉ መጠቀም አልተቻለምና ከዚህ በላይ…
