የሌማት ትሩፋት የዜጎችን ሥርዓተ-ምግብ በማሻሻል የተረጋጋ የገበያ አቅርቦት መፍጠር አስችሏል – ግብርና ሚኒስቴር
የሌማት ትሩፋት የዜጎችን ሥርዓተ-ምግብ በማሻሻል የተረጋጋ የገበያ አቅርቦትና ፍላጎትን በመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እያበረከተ እንደሚገኝ ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያም በተደጋጋሚ በሚያጋጥሟት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በርካታ ዜጎቿ ለችግር ይዳረጉ እንደነበር ይታወቃል። ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተለያዩ ኢኒሼቲፎች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። ከዚህ ውስጥም የሌማት ትሩፋት መርኃ-ግብር አንዱ ሲሆን ዓላማውም የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥና ክብርን ማስጠበቅ ነው። መርኃ-ግብሩ…
