አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የሀገር ፍቅርን ደርባችሁ፣ ለብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት መስራት ይገባችኋል፦አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት እንዲወከሉ አዲስ ለተሾሙ አምባሳደሮች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፥ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የሀገር ፍቅርን በማስቀደም በህዝብ የታመነ አደራን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። አምባሳደሮቹ እውቀትን ከሀገር ፍቅር ደርበው፣ ለብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት የአገልጋይነት ክብርን ማሳየት እንደሚገባቸውም አምባሳደር ታዬ ገልፀዋል። ስልጠናው ሀገሪቱ ከምታራምደው የውጭ ግንኙነት…
