የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰግድ መኮንን ለመንግስት ጸጥታ ሃይሎች እጁን ሰጠ
በአማራ ክልል በርካታ የታጣቂ ቡድን አባላት እና አመራሮች በመንግስት የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው ሰላማዊ ሕይወት እየመሩ መሆኑን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል እንዳስታወቀው÷በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩትን የፀጥታ ችግሮች በንግግርና በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በመንግስት ለታጣቂ ቡድን አባላት እና አመራሮች በተደጋጋሚ የሰላም አማራጮች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ ይሁንና በክልሎችም…
