ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክርቤቱ አባላት ባቀረቡት የ6 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት በማህበራዊ ልማት ዘርፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል ፡፡ከእነዚህም መካከል
የትምህርት ለትውልድ ኢንሼትቭ ስራዎችን ውጤታማ ለማደረግ በጥሬ ገንዘብ፣ በአይነት እና በጉልበት 142,146,033 ብር ተሰብስቧል፡፡ የቱልጊት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉና በክልሉ መንግስት ድጋፍ እየተገነባ ሲሆን ግንባታዉ ከ 90% በላይ ማድረስ ተችሏል፡፡ የትምህርት ተሳትፎ ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል 734,496 ተማሪዎች በመማር ላይ መሆናቸው፡፡ የአንደኛ ደረጃ መማሪያ መጽሐፍ በህብረተሰብ ተሳትፎ ብር 161,205,719 እና…
