February 2025
በፓርቲያችን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንዲሳኩ አመራሩና አባሉ በቁርጠኝነት መስራት ይገባቸዋል፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ”ከቃል እስከ ባህል”በሚል መሪ ቃል በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው። ውይይቱ በጉባዔው በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ትግበራ ለመግባት ዓላማ ያደረገ ነው። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ብልጽግና…
ክልላዊ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን ከሰው ንክኪ ውጭ በሆነ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ መደረግም አለበት።ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በታርጫ ከተማ እየመከረ ነው ። በምክክር መድረኩ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት መልዕክት በግማሽ ዓመቱ የተሻለ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል ። በገቢ አሰባሰብ ሂደት ውስጥ የተገኘውን ጥንካሬ ማስቀጠልና በድክመት የታየውን በመቅረፍ ባለድርሻ አካላት ለገቢ…
በህገ ወጥ መንገድ በባጃጅ ሲዘዋወር የነበረ ቤንዚን መያዙን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ተስፋዬ አበበ ለክልሉ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን እንደገለፁት በቦንጋ ከተማ ዩንቨርስቲ ቀጠና ቦንጋ ግብርና ምርምር አከባቢ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሸ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-01986 ደም ባለሶስት እግር ባጃጅ ከጎጀብ ወደ ቦንጋ ከተማ ለማስገባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል፡፡ በህገ-ወጥ መንገድ…
የክልሉ ምክር ቤት የተለያዩ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።
የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ በተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ የምክር ቤቱን ሁለት ቀናት ውሎ አስመልክቶ ማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተዋል ፡፡ አፈ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ በሰጡት ማጠቃለያ ሀሳብ በክልሉ በአስፈጻሚ ተቋማት የተሻሉ አፈጻጸሞች መኖራቸውን አመላክተዋል ፡፡ ዋና አፈ ጉባዔዉ ከአስፈጻሚ ተቋማት አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ፣ጤና ቢሮ፣ገቢዎችና ሴቶችህ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ተቀናጅተዉ እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። በጤና…
ምክር ቤቱ የቀረቡለትን የዳኞች ሹመቶችን አጽድቋል፡፡
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያም በፍርድ ቤቱ በምልመላና መረጣ ሂደት መሰረት መስፈርትና መረጃዎችን ያሟሉ 46 ዕጩ ዳኞችን ለምክር ቤቱ እንዲሾሙ አቅርበዋል ፡፡ በቀረበው የዳኞች ሹመት 1.ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት 8፣ 2.ለከፍተኛ ፍርድቤት 11፣ 3.ለወረዳና ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤቶች 27 በድምሩ 46 ዕጩ ዳኞች በፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ዳኞች ሆነው እንዲሾሙ ቀርበዋል ፡፡…
የክልሉ ምክርቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል ፡፡
ምክር ቤቱ በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አቅራቢነት የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትዎርክ የሚመሩ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እንዲሆኑ የቀረቡትን ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ፡፡ በዚህም መሠረት 1.አቶ ፍቅሬ አማን፣የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ 2.አቶ ነጋ አበራ፣ምክትል ሰብሳቢ 3.አቶ ፋጂዮ ሳፒ ፣አባል 4.አቶ የሺዋስ ዓለሙ፣አባል 5.ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ፣አባል 6.አቶ አንድነት አሸናፊ፣አባል 7.አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ፣አባል ሆነዉ ተሹመዋል፤በምክር…
ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አቅራቢነት የቀረቡትን 1/አቶ ፍቅሬ አማን የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ 2/አቶ ነጋ አበራ የክልሉ መንግስት ረዳት የመንግስት ተጠሪ 3/አቶ መንግስቱ መኩሪያ የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትዎርክ ስራ አስኪያጅ ሆነው እንዲያገለግሉ ቀረበውን ሹመት የምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል ፡፡ በታጠቅ አበበ
በክልሉ በስድስት ወራት ውጤታማ ተግባራት ተከናዉነዋል።ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)
ምክርቤቱ በ2ኛው ውሎ በአስፈጻሚ ተቋማት በቀረበው የ6 ወራት አፈጻጸም ላይ በተነሱ አስተያየትና ጥያቄዎች ዙሪያ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ በክልሉ በኢኮኖሚው፣በማህበራዊ ልማት ስራዎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል ፡፡ የልማት ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግም መላው ህብረተሰቡን…
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የመረጃ ሥርዓት የዘመነ የህብረተሰቡን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆን ይገባዋል፦ አቶ ታከለ ታምሩ።
በካፋ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አመቻችነት በዞኑ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች የመረጃ ሥርዓት ከማዘመን አኳያ በሚታዩ ተግዳሮቶችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የጋራ ውይይትና ምክክር መድረክ አካሂዷል ፡፡ የካፋ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ታከለ ታምሩ በመክፈቻ ንግግራቸው የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት የመረጃ ሥርዓት የዘመነ፣ ችግር ፈቺና የህብረተሰቡን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆን ይገባቸዋል…
