የክልሉ የኢኮኖሚ ክላስተር የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተገኙበት እየተገመገመ ይገኛል። በዚህም የኢኮኖሚ ክላስተር ስር የሚገኙ ተቋማት የገቢዎች ቢሮ፣የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ፣የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ፣የደን፣አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ፣የግብርና ቢሮ፣የፋይናንስ ቢሮ፣ እንዲሁም የስራና ክህሎት…

Read More

የክልሉ ኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል በየጊዜው በሚያካሂዳቸው ግምገማዎች እና በሚያስቀምጣቸው አቅጣጫዎች በኦዲት ግኝት ላይ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነዉ ፦ የተከበሩ ዋና -አፈጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ እና የክልሉ ምክር ቤት በጋራ አዘጋጅነት የኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል እና ባለድርሻ አካላት ጋር የኦዲት በጀት አፈጻጸም በአመያ ከተማ እየገመገመ ነዉ። የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ የአፈጻጸም ግምገማውን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ፣የክልሉ ኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል አጠቃላይ 14 አባላትን ያቀፈና በክልሉ ምክር ቤት አስተባባሪነት የኦዲት ግኝት…

Read More

ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣች ነው- በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የጀመረችው ሪፎርም በዓለም አቀፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መመዘኛ የተሻለ ደረጃ ላይ እንድትገኝ ማስቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሚኒስትሮች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት እየተገመገመ ነው። በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት የለውጡ መንግሥት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ጨምሮ በርካታ የሪፎርም ሥራዎችን…

Read More

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በመሰረተ ልማት ትብብራቸው ዙሪያ ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ የመሰረተ-ልማትና ኢክዩፕመንት ሚኒስትር ሀሰን ሀሙድ ኢብራሒም ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም ሁለቱን አገራት በመሠረተ-ልማት ለማስተሳሰር የተጀመረው የዲኪል-ጋላፊ መንገድ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደት እና በቀጣይ ምዕራፍ የሚሰሩ ስራዎች ላይ መክረዋል። በተጨማሪም በቅርቡ በአራቱ የቀጣናው ሀገራት ስምምነት ይፋ የሆነው የኮሪደር ማኔጅመንት ባለስልጣን በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና የአፍሪካ…

Read More

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ የገጠርና ከተማ ዕድገት ማመጣጠን እንደሚገባ ተጠቆመ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ በልዩ ልዩ የኢንዱስትሪ ስትራቴጅዎችና ፖሊሲዎች ፤በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን እና ዲጂታላይዜሽን ላይ ለካፋ ዞን የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ የገጠርና ከተማ ዕድገት ማመጣጠን እንደሚገባ የገለጹት የቢሮው ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ ስልጠናው የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች የመንግሥት ዓላማና ተልዕኮ ለመፈጸም ግንዛቤ የሚያሳድግ እንደሆነ ተናግረዋል።…

Read More

በክልሉ የገጠር ትስስር ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና (RCFS) ፕሮግራም የስትሪንግ ኮሚቴ በሚዛን አማን ከተማ ውይይት አካሂዷል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንደገለፁት ክልሉ ከተቋቋመ ጥቂት ዓመታት መሆኑን ጠቁመው ከቀድሞው ክልል የተረከባቸው በርካታ የመሠረተ ልማት ዕዳዎች መኖራቸውን ተናግረዋል ። የክልሉን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የተመቻቸ ለማድረግ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን ምቹ ሁኔታ መፍጠር የግድ በመሆኑ መንግስት አቅዶ ከሚሰራው ባሻገር…

Read More

የውስጠ ፓርቲ አንድነትን በማጠናከር የብልጽግና ፓርቲ ጉዞን እውን ለማድረግ አመራሩ እና አባሉ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የቴፒ ብዝሃ ማዕከል የክልል ሴክተር የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ በቴፒ ከተማ አካሂዷል። በአባላት ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት ቴፒ ብዝሃ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ደምሴ ደንቦ የፓርቲውን አሰራሮች እና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የውስጠ ፓርቲ አንድነትን በማጉላት ተግባራትን የመምራት…

Read More

የወጪ ንግድ ዘርፍ አፈጻጸምን በዓመቱ መጨረሻ 7 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ እየተሰራ ነው፦ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

የወጪ ንግድ ዘርፍ አፈጻጸም ባለፉት 9 ወራት ከተመዘገበው 5 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር በዓመቱ መጨረሻ 7 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አፈፃፀም የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ካሳሁን ጎፌ…

Read More

ባለፋት ዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ያለፉት ዘጠኝ ወራት የቡና ንግድ አፈፃፀምን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ባለፋት ዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት 299 ሺህ 607 ቶን ቡና በመላክ ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻሉንም ጠቅሰው፤…

Read More

የመንግሥት ተቋማት ለህዝቡ የሚሰጡት አግልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነትን ያረጋገጠ መሆን አለበት፦ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የመንግሥት ተቋማት ለህዝቡ የሚሰጡት አግልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነትን ያረጋገጠ መሆን እንዳለበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ። የክልሉ ጤና ቢሮ የመንግሥት የጤና ተቋማት አግልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ያተኮረ ክልላዊ ንቅናቄ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በመንግሥትና መሪው የብልጽግና ፓርቲ በልዩ…

Read More