የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመሠረተ ልማት ክላስተር ተቋማት የ9 ወራት የተግባር አፈፃፀም ግምገማ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዋ ሳፒ እንደገለፁት እያደገ የመጣውን የህዝብ የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት የጋራ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይገባል ብለዋል ። በመሰረተ ልማት ክላስተር ሥር ያሉ ተቋማት በዕቅድ አፈፃፀም ያለውን ጥንካሬና ጉድለቶች በመለየት የጋራ አረዳድ በመያዝ ለቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም መዘጋጀት…
