ኮፕ 32 ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም አቅም ለዓለም ለማሳየት የሚረዳ ትልቁ ጉባኤ ይሆናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኮፕ 32ን በውጤታማነት ለማሠናዳት የሚያስችል አቅጣጫ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮፕ 32 ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት ከሚያስችለው የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርገዋል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማስተናገድ ያላትን ቁርጠኝነት በሚያመላክተው በዚህ ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጤታማ ጉባኤን ለማሠናዳት የሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል። ኮፕ 32 ጉባኤን ለሀገር ግንባታ እና ለገጽታ ግንባታ…
