የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች ላይ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን እየተካሄደ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ የለውጡ መንግስት ለንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት የፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የክልሉን ኢንቨስትመንት በመለየት፣ በማጥናት እና ልማታዊ ባለሀብቶችን በመደገፍ በዘርፉ ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን መቻሉን በመክፈቻ ንግግራቸው አንስተዋል። በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመለየትና በማጥናት በዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የሀገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በትኩረት…
