የአመራር ውጤታማነትን በየደረጃው ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት አስታወቀ።
በየደረጃው ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ችግር ፈቺ ምላሽ ከመስጠት አንጻር የሚስተዋለውን ክፍተት ለማረም የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጠባቸው ፓርቲው አመላክቷል ። የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ አማካሪ አቶ አለማየሁ አይበራ የመንግስትን እና የፓርቲ ስራዎች የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሥራ ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመላከቱት ተልዕኮውን በብቃት መምራት የሚችል…
