የመደመር መንግስት የሀይማኖት ተቋማት ለሀገርና ለትውልድ ግንባታ የከፈሉትን ዋጋ በሚገባ በመረዳት እውቅና ይሰጣል፦ አቶ አልማው ዘውዴ
የመደመር መንግሥትና የሀይማኖት ተቋማት በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የሙስሊም አባቶች ውይይት በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በውይይት መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የመደመር መንግስትና የሀይማኖት ተቋማት ሚና በሚል መሪ ቃል በየደረጃ ካሉ የሀይማኖት መሪዎች ጋር ሰፊ ውይይቶችና ምክክሮች እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገራችን…
