የክልሉ ፀጋዎችን በአግባቡ በማልማት ኢኮኖሚ የማመንጨት አቅማቸውን ማሳደግ ላይ ትኩረት መደረጉን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ገለፀ።
የክልሉ መንግስትና የፓርቲ 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የክልሉን መንግስት የ9 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማትና ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ በተለይ የኢኮኖሚ ክላስተር አፈፃፀሙን በዳሰሰው ሪፖርታቸው ግብርና የክልሉ ትልቁ ፀጋ በመሆን ዘርፉን በማሻሻልና በማዘመን የህብረተሰቡን…
