የመንግስትን ሀብትና ንብረት ከብክነት ለመከላከል ለውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች በቂ አቅም መፍጠር እንደሚገባ ተጠቆመ
ከክልሉ ወረዳዎች ለተውጣጡ የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል። የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ እንደተናገሩት፣ስልጠናው የውስጥ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን ላይ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ የፋይናንስ ዘርፍ አሰራር ስርዓቱን ለማሳደግ ያለመ ነው ብለዋል። በክልሉ ለሚገኙ የውስጥ ኦዲት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አቅም በመፍጠር ክትትልና ድጋፍ በማድረግና በማስተባበር ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ ስራ…
