የ2017 የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
እንኳን ለ2017 ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን የገለፁት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዎኖ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ የአደባባይ በአላት አንዱ የሆነዉ የከተራና የጥምቀት በዓላት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደስራ መገባቱን ተናግረዋል። በክልሉ በስድስቱም ዞኖች፣ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች 850 ታቦታት እንዳሉ…
