BLOGS
በክልሉ በተገኘው ሠላም፣ የገጠርና የከተማ የኢንቨስትመንት ፍሰት በእጅጉ ጨምሯል፦ አቶ አንድነት አሸናፊ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ “ዘላቂ ሠላም ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መር ቃል የ2016 ዓ/ም ዕቅድ አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ የሴክተር ጉባኤ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በክልሉ ዘላቂ ሠላምና በማስፈን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በ2016 በጀት ዓመት የባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤት መመዝገብ ነው የክልሉ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ…
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተግባሪ ወረዳዎች ጋር የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ/ም እቅድ ዙሪያ ምክክር አድርጓል ።
በሰቆጣ ቃልኪዳን የህጻናት መቀንጨር ከምግብ ስርአት ጋር ተያይዞ በርከት ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡም ታውቋል ፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተግባሪ ወረዳዎች ጋር የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ/ም እቅድ ዙሪያ በሚዛን አማን ከተማ ምክክር አድርጓል ። በክልሉ ጤና ቢሮ…
በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ሂደት የሚከናወኑ ስራዎችን እንደግፋለን – የተመድ ድርጅቶች
በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ሂደት የሚከናወኑ ተግባራትን እንደሚደግፉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ተቋማት ገለጹ። የድርጅቶቹ ተወካዮች በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ስራዎችን መደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ ተገኝተዋል። የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) መንግስት…
በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም የ3 ጊዜ የሞት ፍርደኛ እንደነበር ፖሊስ አስታወቀ
ሰሞኑን በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ፣ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም 3 ጊዜ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት እንደነበር ፖሊስ ገልጿል፡፡ ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ እንደተቻለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታሕሳስ 25 ቀን 1999…
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢትዮጵያን ምርት የመግዛት ባህል ማዳበር ያሰፈልጋል፦ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢትዮጵያን ምርት የመግዛት ባህል ማዳበር ይገባል ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ ካዘጋጀው የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽን ጎን ለጎን ትኩረቱን የጥራት መሰረተ ልማት ላይ ያደረገ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት፤ ጥራት ለምርቶች…
ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እና ከጋምቤላ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ለተውጣጡ ዲኖች ፣ አሰልጣኞችና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ዞኑ በተፈጥሮ ሀብቱ የበለፀገ በተለይም በተፈጥሮ ደን፣ በቱሪስት መስህቦች፣ ቡናና ቅመማ ቅመም፣ በማርና በሻይ ምርት የሚታወቅና ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ብሎም ኤክስፖርት በማድረግ ከአካባቢው አልፎ ለሀገር አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም ዞኑ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች…
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ልማት የግሉን ዘርፍ በስፋት እንዲሳተፍ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አገር አቀፍ የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽንን ምክንያት በማድረግ “አረንጓዴ ኢኮኖሚን እውን በማደረግ ሂደት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሚና “በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት አካሂዷል። ከውይይቱ ጎን ለጎንም በኃይል ቁጠባ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡና፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሽያጭ የፈጸሙ ኩባንያዎችና ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷል። በሥነ-ስርዓቱ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶክተር)፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰሃረላ…
