የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጡን እንዲያጎለብት የሚያግዙ ድጋፎች እየተደረጉ እንደሚገኝ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለጹ
የሆስፒታሉን ተግባር አፈጻጸም የሚገመግም የቦርድ አባላት የጋራ ውይይት ተካሂዷል። የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ዳዊት ገበየሁ በውይይቱ ላይ እንዳሉት ሆሲፒታሉ አገልግሎቱን እንዲያሳልጥ የሚያግዝ ድጋፍ በተገቢ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። ሆስፒታሉ ከሚሰጠው የአገልግሎት ስፋትና ከግብአት አቅርቦት አኳያ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት እየተሰራ እንደሚገኝም ዋና አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል። የ9 ወራት የሥራ ሪፖርት ያቀረቡት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ…
