የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ አመራሮች ካውንስል ተመሠረተ
በዚሁ ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እንደተናገሩት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሀገራዊ ልማት በመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። ተቋማቱ የክህሎትና የዕውቀት ሽግግር በማድረግ ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተመሳሳይ ተልዕኮ ካላቸው ተቀማት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተደራጀ መልኩ ለማሳለጥ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዘርፉን…
