የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ እንኳን ለቤንች ብሔረሰብ ዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል “ቢስት ባር ” በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
ዋና አፈጉባኤ ወንድሙ ኩርታ የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” መከበሩ ክልሉ ለባህል መጎልበት የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል። የክልሉ መንግስት የብሔሮች ብሔረሰቦች ባህል ጎልቶ እንዲወጣ፣እንዲለማና ጥቅም ላይ እንዲውል በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል በመልዕክታቸው ። የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” ቀደምት አባቶች ያቆዩትና በመሀልም ተረስቶ ለዘመናት ሳይከበር እንደቆየም አስታውሰዉ አሁን…
